Discussion about this post

User's avatar
Mik's avatar

አረ ስቃይ ነው ወንድሜ እኔ ዳሽን ባንክ ውስጥ ነው የምሰራው ፡ይኸው 2 ዓመት ሞላኝ አዲስ ደንበኛ ማምጣት (Account Opening ) የግድ በሳምንት ውስጥ የሚሰጥህ ቁጥር አለ እሱን መሙላት አለበት አለበለዚያ ከደሞዝ ቅጣት ጀምሮ በፐርሰንት እስከ የመጨረሻ የፅሁፍ ማስጠንቀያ ድረስ በዚህ ጉዳይ ብቻ ይደርስሀል ፡ ከዛ እንደምንም እሱን ተወጣው ስትል ደሞ ያስከፈትካቸው አካውንቶች ዲፕዚት በኳርተር ተብለህ ይሄን ያህል ሚሊዮን ብር ማምጣት አለብህ ፡ አለበለዚያ ያው ከዲስትሪክት ጀምሮ የብራንቹ ማናጀር ድረስ አንተ ላይ ነው ዱላው ፡ በዚህ አጋጣሚ አይነ ውሀህ ካልተመቸው ብራንች ማናጀሩ አዲስ ደንበኛ ስላላመጣህ በበቂ ሁኔታ እና Deposit በቂ ስላላመጣህ ተብዬ ደብዳቤ ተፅፎብኝ እኔው እራሴ ከ 5ወር በፊት ይኸው አሁን ባየው ባየው የሚዘለቅ አለመሆኑ ሲገባኝ መልቀቂያ አስገብቻለሁ ፡ በፈቃዴ ስራውን ልለቅ በዚህ ምክንያት፡፡ ቀጣይ ምን እንደምሰራ እራሱ ግራ ግብት ብሎኛል ፡ በቤት ኪራይ ነው የምኖረው፡ ዕድሜዬ 29 ነው ፡ በቢዝነስ ማኔጅመንት ዲግሪ አለኝ ፡ እንዲሁም Master Of Business Adminstration (MBA) ማስተርስ አለኝ ፡ ከንቱ ልፍት ሆነብኝ ይኼ ሁሉ ዓመት አፈር ድሜ በልቼ ፡ ስራ እየሰራው እራሴን አስተምሬ ፡ ይኸው ሆነ የድካሜ ፡ ውጤት ፡ በጣም ያሳዝናል ። እረጅም ጊዜ ሌሊት ሁሉ ጭምር አሁን ከየት ነው አዲስ ደንበኛ የማገኘው፡ዲፖሲትስ ማን ይኼን ሁሉ ሚሊዮን ብር አለኝ ብሎ ባንኩ ላዮ Deposit የሚያደርገው እያልኩ ከልክ በላይ በመጨነቄ የተነሳ Mental Stress ታምሜ ህክምና እየተከታተልኩ ነው ፡የመንግስት ሆስፒታል፡ ፈጣሪ በሚያውቀው፡ በዚህ ደረጃ ነው ችግሩ ያለው ለማለት ነው፡መሰረት ከልብ እናመሰግናለን የልባችንን፡ሰው እንዲያውቅልን ስላደረስክልንThank You So Much ዕድሜና ጤና ይስጥህ !!!

Expand full comment
Anbesawdm's avatar

መሠረት ከልብ እናመሠግናለን እኔ የአዋሽ ባንክ ሠራተኛ ነኝ በግል በገኝህና የሠራተኝነት መረጃዎቼን አሣይቼህ ቃሌን በ audio ጭምር ብሠጥ ደስ ይለኛል ። እዚ ቤተሠብ ያለን ሠዎች ተምረን የልመና ስራ ከምንሠራ ብለን እየለቀቅን ነው አዋሽ ባንክ ሠራተኞቹን ልመና መሣራት ጀምሮዋል። ጥያቄ ስንጠይቅ ስራ አጥ ሞልቶዋል ካልፈለጋቹ ልቀቁ ነው ሚሉን ከባለ ሞያነት ወደ ባርያነት ቀይረውናል።

Expand full comment
6 more comments...

No posts