(መሠረት ሚድያ)- ኢትዮጵያ ከአለም አቀፍ አበዳሪ ተቋማት ገንዘብ በማግኘት በአባይ ወንዝ ላይ የሀይድሮ ኤሌክትሪክ ግድብ ለመገንባት ለበርካታ አመታት ብዙ ሙከራ አድርጋ የነበረ ቢሆንም በግብፅ ተፅእኖ አለመሳካቱ ይታወቃል።
በዚህም ምክንያት የዛሬ 13 አመት የህዳሴ ግድብን በራስ ወጪ ለመገንባት እቅድ ተነድፎ እንቅስቃሴ መጀመሩን መንግስት ገልፆ ነበር።
ከአርሶ አደር እስከ ነጋዴ፣ ከመንግስት ሰራተኛ እስከ ዳያስፖራ ጭምር ለዚህ ግድብ ድጋፍ አድርሶ አሁን ያለበት ደረጃ ላይ ደርሷል።
ይሁንና በርካታ አነጋጋሪ፣ ያልተረጋገጠ እንዲሁም አንዳንዴ ሀሰተኛ መረጃ ሲያሰራጩ የሚታዩት የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናናድ ትረምፕ ዛሬ ደግሞ ሀገራቸው አሜሪካ የህዳሴ ግድብን ፋይናስ እንዳደረገች የሚገልፅ መረጃ 'Truth Social' በተባለ የራሳቸው የሶሻል ሚድያ ፕላትፎርም ላይ ለጥፈዋል።
ፕሬዝደንቱ በርዋንዳ እና ኮንጎ፣ በህንድ እና ፓኪስታን፣ በሰርቢያ እና በኮሶቮ እንዲሁም በግብፅ እና በኢትዮጵያ መሀል ጦርነት እንዳይቀሰቀስ ማረጋቸውን ጠቅሰው ለዚህም የኖቤል የሰላም ሽልማት ቢገባቸውም እንዳልተሰጣቸው ፅፈዋል።
አክለውም ስለ ህዳሴ ግድብ ሲፅፉ "ኢትዮጵያ እየገነባችው ያለው ግዙፍ ግድብ አለ፣ በጅልነት በአሜሪካ ፋይናንስ የተደረገ ነው፣ ወደ ናይል የሚፈሰው ውሀ በከፍተኛ ደረጃ እንዲቀንስ የሚያደርግ ነው" ብለዋል።
መሠረት ሚድያ ያገላበጣቸው በርካታ የሀገር ውስጥ እና አለም አቀፍ ሰነዶች የህዳሴ ግድብ ከጥቂት የቻይና መንግስት አስተዋፅኦ ውጪ በኢትዮጵያ ህዝብ እና መንግስት ወጪ እንደተገነባ ያሳያሉ።
ለማሳያነት ከሀገር ውስጥ የቦንድ ሽያጭ እና ከዜጎች መዋጮ እስከ 450 ሚልዮን ዶላር፣ የባለሀብቶች ተሳትፎ 88 ሚልዮን ዶላር ገደማ፣ የቻይና ብድር 2.2 ቢልዮን ዶላር እንዲሁም ዋናው ከመንግስት ወጪ 5 ቢልዮን ዶላር ገደማ እንደሆነ መረጃዎች ያሳያሉ።
ፕሬዝደንት ትረምፕ የፃፉት መረጃ ሀሰት የመሆኑ አንድ ማሳያ ግብፅ እና ኢትዮጵያ ስምምነት ላይ መድረስ ባለመቻላቸው የዛሬ አምስት አመት አሜሪካ ለኢትዮጵያ ከምትሰጠው ሰብአዊ እርዳታ ላይ 100 ሚልዮን ዶላር መቀነሷ ነው።
አሜሪካ ለግድቡ የምታደርገው ድጋፍ ባለመኖሩ ያቋረጠችው የህዳሴ ግድብ ድጋፍን ሳይሆን አሜሪካ ለኢትዮጵያ በአጠቃላይ ከምትሰጠው እርዳታ ላይ ነበር። ግብፅ ባደረገችው ተፅእኖ የህዳሴ ግድብ በኢትዮጵያውያን አቅም እንደተገነባ የሚያሳየው ይህ ሰፋ ያለ አለም አቀፍ ዳሰሳ አንዱ ነው (ሊንክ: https://link.springer.com/chapter/10.1007/978-3-319-97094-3_11)
ከዚህ ውጪ ቻይና የዛሬ አስር አመት ገደማ ለሀይል ማስተላለፊያ መስመር ግንባታ የ1.2 ቢልዮን ዶላር ብድር ለኢትዮጵያ ሰጥታ ነበር (ማስረጃ: https://www.disruptionbanking.com/2023/09/04/why-is-china-financing-the-grand-ethiopian-renaissance-dam-gerd/?utm_source=chatgpt.com)
ከዚህም በተጨማሪ የቻይናው 'Exim Bank' ለተርባይን እና የኤሌክትሪክ ተከላ ተጨማሪ 1 ቢልዮን ዶላር ብድር ለኢትዮጵያ ሰጥቶ ነበር።
የህዳሴ ግድብ በአምስት አመታት ውስጥ በ4.6 ቢልዮን ብር ገደማ ወጪ ይጠናቀቃል ተብሎ ቢጀመርም በበርካታ ምክንያቶች ተጓቶ በመጨረሻም በመጪው መስከረም ለምርቃት እንደሚበቃ ይጠበቃል።
መረጃን ከመሠረት!
President Donald Trump has celebrated his 79th birthday very recently, if forgets some issues is quite acceptable