Discussion about this post

User's avatar
Dr. Aschalew's avatar

መሰረት ሚዲያን ለዘገባው እናመሰግናለን

የውጭ አገር ስራ ስምሪት ላይ እየተፈፀመ ያለው ብዝበዛ በተለይም በመስሪያ ቤቱ ለሲስተም ማበልፀግ ፕሮጀክት በተቀጠሩት ሰራኞች እጅግ አስገራሚና አይን ያወጣ ነገር ነው፡፡ ሲስተሙን በመጀመሪያ ደረጃ የመረጃና ደህንነት ኤጀንሲ የሚባለው ኢንሳ እራሱ የሚያውቀው አይመስልም፡፡ የዛሬ አመት አካባቢ 18000 የሚሆኑ ዜጎች እዚህ ሲስተም ላይ አድሚን በሆኑና ፕሮጀክቱን በሚመሩ ሰዎች አማካኝነት ህገወጥ የኢሚግሬሽን ማለፊያ ወይም ኪው አር መውጣቱ ኦዲት ላይ ተረጋግጦ ሳለ ሚንስትሯ በነዚህ ሰዎች ላይ ምንም እርምጃ አለመውሰዷ የጥቅም ቁርኝት እንዳላቸው ያሳብቃል፡፡ አሁን ደግሞ ይባስ ብሎ ከዚህ በፊት በመ/ቤቱ በመሪ ስራ አስፈፃሚነት ደረጃ የነበሩትን ሴት ለሲስተም ክፍሉ አልታዘዝም በማለታቸው ምክንያት ከስራቸው በማባረር፣ የሲስተም ክፍሉን ቡድን ሲመራ የነበረ ለቦታው በቂ የትምህርት ዝግጅት ቢኖረው እንኳን ቦታው የሚፈልገውን የስራ ልምድ የሌለውን ሰው ሚንስትሯ በመሾም እነሱ የሚፈልጉትን ብቻ ለማስፈፀም እየሞከሩ እንደሆነ አይተንበታል፡፡ ይህ ግለሰብ ቦታውን ከያዘ ጀምሮ በየእለቱ የተለጠፉ ማስታወቂያዎች ብዛት የመ/ቤቱም ግድግዳ የቻለው አይመስልም፡፡ አንድን ትልቅ ሴክተር ከመመሪያ ይልቅ ማስታወቂያ እየመራው ነው ብንል ይቀላል፡፡

Expand full comment
Fantu didha's avatar

ይህ ዘርፍ አዋጅና መመርያ ቢወጣለትም ጠያቂ በሌለው ሚ/ር መ/ቤቱ ማዘዝ እንጂ ማዳመጥ በመይወዱት ሚንስትሯ ማን እና ምን እንደሆነ በማይታወቅ አካል (ስምና ሀላፊነቱ ተጠቅሶ በማይታወቅ አካል የየቀን የግድግዳ ላይ ማስታወቅያ) የሚመራ በዚህ አካሄድም እየጠፋ ያለ ዘርፍ ነው

እኔ በዚህ ዘርፍ ላይ ከአምስት በላይ ሚኒስትሮችን አውቃለሁ ህግና ደንቡ በየሚንስትሩ ልክ ሲሻሻልም አውቃለሁ ነገር ግን በማንም የአስተዳደር ጊዜ ስምና ሀላፊነቱ በማይታወቅ አካል ፍላጎትና ስሜት ሲመራ ሳይ የመጀመርያዬ ነው

እንደሀገር ሚ/ር/መ/ቤቱ እያከናወነ ያለው ነገር ያማል ሙሉለሙሉ በሚባል ደረጃ ሚናውን ስቷል አንዴ ትኬት ካልቸረቸርኩ በሚል ሲስተሙን በመዝጋት ለበረራ የተዘጋጁ ልጆችን ሲያንከራትት ሌላ ጊዜ ልጆቹን እኔ መልምዬ ለኤጀንሲዎች ካልሰጠሁ እያለ የበረሩ ልጆችን ሳይቀር ለኤጀንሲዎች እየበተነ ከተማዉን የማያውቁ ልጆችን ሲያንከራትት ስራውን ሲያስተጓጉል ዘርፉን ለማጥፋት ቆርጦ የተነሳ እንጂ ዘርፉን ለማዘመን ያሰበ አይመስልም

ከዚህ ሁሉ በላይ ጥያቄ ያነሳ የዘርፉ ባለቤት የሚደርስበትን ስለሚያውቅ ሚ/ር/መ/ቤቱ ዘርፉን ከማዘጋቱ በፊት የቻልኩትን ያህል ልስራ በሚል ተስፋ መቁረጥ ሚ/ር/መ/ቤቱ ግድግዳ ላይ በሚለጠፍ ቁራጭ ወረቀት ቀጭን በማስፈራርያ የታጀበ ማስታወቅያ መሠረት መስመሩን ሳይስት ለመሄድ እየሞከረ ይገኛል

የሚያሳዝነው ግን የሁል ጊዜ በግፅ ኤጀንሲዎች በዝታቹዋል መቀነስ አለባቹ (100 ኤጀንሲዎች ብቻ!!! )የሚለው አይን ያወጣ በማን አለብኝነት ያሸበረቀ የሚ/ር/መ/ቤቱ ግልፅ አቋም ምንም እንኳን አዲስ ፍቃድ አቆምኩኝ ቢልም በጎን በድብቅ የሚሰጣቸው አዳዲስ ፍቃዶች መብዛትን ላስተዋለ 100ዎቹ ሚ/ር/መ/ቤቱ የሚፈልጋቸው ኤጀንሲዎች ሲሞሉ አሁን ያሉትን ሙሉ ኤጀንሲዎች በተለመደ ማንአለብኝነት እንደሚያግድ እና ከስራ ውጭ እንደሚያደርጋቸው ግልፅ ይሆንለታል።

ለዚህም ማሳያው ትላንት ያወጣው ከ100 በላይ ኤጀንሲዎችን የማገድ ስራ በቂ ማስረጃ ነው

ስለዚህ ሚ/ር/መ/ቤት አሰራር ግድፈቶች አይደለም በአስተያየት በእድሜዬ ልክ ፅፌ የማልጨርሰው በመሆኑ አዝናለሁ

ሰሚ ካለ ግን ይህ ዘርፍ ለሀገሬ በእጅጉ የሚያስፈልጋት ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች የምታገኝበት በመሆኑ አንዴ ከተዘጋ ክብርት ሚኒስትሯ (ይዘጋ እናሰማ ከፍተዋለን!) እንደሚሉት ቀላል አይሆንም ምክንያቱም በሀገር ያለን የስራ እድል ልክ እን ኤጀንሲው እንደፈለጉ መክፈትና መዝጋት ቀላል አይደለም

Expand full comment
2 more comments...

No posts