(መሠረት ሚድያ)- የውጭ ሃገር የስራ ስምሪት አዲሱን ረቂቅ አዋጅ በተመለከ የወጣውን መረጃ አንብበናል።
በመረጃው የተነሱ ሃሳቦች ላይ መረጃ ከመስጠቴ በፊት የውጭ ሃገር የስራ ስምሪት አዋጅ ከ30 ዓመት በላይ ሴት ልጆቻችን አረብ ሃገር ሲገደሉ፣ እንቅልፍ አጥተው ሰርተው… በባዶእጃቸው ወደ ሃገራቸው እንደ ሌባ ተቆጥረው ሲባረሩ፣ ጤነኛ ሆነው ሄደው አካላቸው ጎድሎ ሲመለሱ በየበርሃው የፈሳሳው ደማቸው፣ በየሰው ቤት ያንቡት እንባ... ብዙ... ብዙ... ስቃያቸው የሚታበስበት እና ዜጎች መብታቸው፣ ደህንነትቻው እና ጥቅማቸው ተጠብቆ እንዲሰማሩ የሚያደርግ አዋጅ ነው።
እንዴት ? ምን ማለት ነው። የሚል ጥያቄ ሊኖር ይችላል !! በ ሚዲያችሁ በተጋራው የመረጃ Frame መሰረት ሃሳቤን ላስቀምጥ!
1) ሰራተኛ ወደ ውጭ ሃገር የስራ ስምሪት የሚያሰማራ ማንኛውም ኤጀንሲ ፍቃድ ከመውሰዱ በፊት ለዜጎች ደህንነት ዋስትና የሚሆን 100,000 ዶለር በባንኮች በዝግ አካውንት እንዳይንቀሳቀስ ያስቀምጣል። የሚል ቀድም ሲል የወጣ አዋጅላይ ስለተቀመጠው አንቀጽ…
ይሄ ገንዘብ ዜጎች ደሞዝ ባይከፈላቸው... በካሳ መልክ ለመክፈል፣ ጉዳት ቢደርስባቸው... የሚገባቸውን ካሳ ለመክፈል፣ ቢታመሙ... ለማሳከም፣ ዜጎች የላካቸው ኤጀንሲ ወደ ሃገር እንዲመልሳቸው ሲጠይቁ እምቢ ቢል... ትኬት ቆርጦ ለመመለስ። በአጠቃላይ የዜጎችን ደህንነት ለመጠበቅ በሚንስቴር መስሪያ ቤት ትህዛዝ ይሄንን ለመፈጸም የሚውል ካሽ ገንዘብ ነው።
ይሄ ገንዘብ ባንክ ተቀምጧል ወይ ? አጄንሲዎች ከባንኮች ማናጀሮች ጋር በፈጠሩት የጥቅም ትስስር ባንኮች በዝግ አካውንት እንደተቀመጠው አድርገው ሃሰተኛ ደብዳቤ እና የባንክ ስቴትመንት ለኤጀንሲዎች በመስጠት የተቀመጠው ገንዘብ ሲጣራ ከ10% በታች ኤጀንሲ ብቻ ማስቀመጡ ተረጋግጦል።
ባንኮች ገና ለገና ኤጀንሲዎች ዜጎቻችን አረብ ሃገር ሄደው ዶላር ያመጡልናል በሚልና በገንዘብ የተደለሉ ማናጆሮች በሚሰጡት ማስረጃ የተላኩ ዜጎች በባርነት ወደ ኢራቅና ሶሪያ ቢልኳቸው ምንም የሚያሰጋቸው ነገር አይኖርም። የሚወረስ ገንዘብ የላቸውም !! ደህንነቱ ያልተጠበቀ ቦታ ልጆቻችን ቢወድቁ የሚያስፍራቸው ነገር የለም። ይሄ ማለት በስቃይ አልፈው ለሃገራቸው የሚበቁ ዜጎችን ለመደጎም የሚሆን በዝግ አካውንት የተቀመጠ ገንዘብ የለም ማለት ነው።
ይህንን ገንዘብ ለዜጎችን ዋስትና በሚሆን መልኩ ወደ ሚንስቴር መስሪያቤቱ አካውንት ይቀመጥ ማለት ይሄንን ችግር ሙሉ ለሙሉ መቅረፍ ይቻላል ማለት ነው። እንደምሳሌ እንኳን ብናይ በተመሳሳይ ዘርፍ እጅግ ስኬታማ የሆኑ ሃገራት የተለመደ የ አሰራር ስርዓት ነው። ምሳሌ ፊሊፒንስ፣ ኬንያም በተወሰነ መልኩ፣ ዑጋንዳ፣ ስሪላንካ እና ሌሎችም...
ስራውን ማቆም እፈልጋለሁ የሚል ማንኛውም ኤጀንሲ ለዜጎች ዋስትና ያስያዘውን ገንዘብ በየትኛውም ጊዜ መውሰድ እንደሚችል ደግሞ ተቀምጧል።
2 የሰለጠኑ ዜጎችን ለኤጀንሲዎች የሚደረግ ምደባን በተመለከተ
አንድ ሰው ወደ ውጭ ሃገር ለስራ የሚያሰማራ ኤጀንሲ በሚልከው በእያንዳንዱ ሰው በትንሹ $900 ዶላር ያገኛል። አብዛኞቹ ኤጀንሲዎች ይሄ ብር አልበቃ ብሏቸው ከደላላ ጋር በመመሳጠር ወደ ውጭ ለስራ ከሚሄድ ሰው በትንሹ ከ60,000 - 80,000 ብር ይቀበላሉ። የሚሄዱ ልጆች ብሩን ቀጥታ ለኤጀንሲው አይሰጡትም ! በደላላው በኩል ነው የሚከፈለው... ብር የከፈሉ ዜጎች ሚንስቴር መስሪያቤት ጋር ጥቆማ በሚሰጡበት ጊዜ ኤጀንሲውንና ልጅቷን ቁጭ አድርገን ስንመርመር ኤጀንሲ ከመስሪያቤቱ በላይ "በነጻ ለሚደረግ ጉዞ ለምን ትክፍያለሽ ብሎ ልጅቷ ላይ በመጮህ ድራም ይሰራል። ይሄ በኤጀንሲዎች የሚደረገው ህገወጥ ተግባር በአብዛኛው ኤጀንሲ የሚፈጸም ነው።
ይሄ ተግባር የሚፈጸመው ለብዙ ዓመታት ደላሎችና በኤጀንሲዎች መካከል ለብዙ ዓመታት የቆየ ትስስር ስላለ ነው። ይሄ ትስስር ካልተበጠሰ ዜጎቻችንን ከብዝበዛ ማዳን አይቻልም ተብሎ ችግሩን ለመፍታት ጥናት ተደርጓል። በዚህ መሰረት ኤጅንሲው ወደ ውጪ ሃገር መላክ በሚፈልገው መስፈርት መሰረት (ተቀባይ ሃገር የሚገኘው ፓርትነር በሚሰጠው መስፈርት መሰረት) ሰልጥነው ከተቀመጡ ዜጎች ውስጥ እንዲውስድ ማድረግ ነው። በዚህ መንገድ ደላላ ያላመጣልትን፣ ገንዘብ አምጪ/ጣ ማለት የማይድፈረውን ሰራተኛ ያጋኛል ማለት ነው።
3 ረቂቅ አዋጁ ላይ የተደረገ ውይ ይትን በተመለከተ
ረቂቁን በተመለከተ ከ ባለድርሻ አካላት ጋር ከክልሎች ጋር እንዲሁም ከ ፹0 በላይ ኤጀንሲዎች ጋር ከሁለት ጊዜ በላይ ተደርጓል። ይሄም ሁሉም የሚመለከተው ባለድርሻ አካል በው ይ ይቱ ተገኝቶ የፈረመበት አ ቴንዳንስ ያለ በመሆኑ ፈጽሞ ሃሰተኛ መረጃ ነው። ዞሮ ዞሮ ብኋላ ረቂቁ ወደ ህግ ከመቀየሩ በፊት የውይይት ሰነዶች መጠየቃቸው ግዴታ ስለሆነ ይሄንን በተመለከተ የተነሳው ሃሳብም ሃሰተኛ ነው።
የውጭ ሃገር የስራ ስምሪት ላይ በመሰረት ሚዲያ የቀረበው ቅሬታ ፈጽሞ ሃሰትና የተነሱ ሃሳቦችም እውነታው እየታወቀ ሆን ተብሎ አንባቢውን ለማሳሳት የተከናወኑ መሆኑ እንዲታወቅ በአክብሮት እንጠይቃለን።
ሚንስቴር መስሪያቤት በአዋጅና በሌሎች የትኛውም ጉዳዮች መወያያት ለሚፈለግ አካል ቢሮ ክፍት መሆኑን በዚሁ አጋጣሚ እንገልጻለን።
አቶ ብርሀኑ አይልካ፣ የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የፕሮጀክት ማናጀር
መረጃን ከመሠረት!
ስለ ኢምግሬሽን ነው የፃፍኩት 😭
ለምን ለሜዲካል ተብሎ ደም ቀዲተዉ እና ኤክስሬ አንስተዉ ለሚሰሩት ስራ 9500ብር ለሚያስከፍሎት እንዲሁም በካሽ ብቻ ነዉ የምናስተናግደዉ በማለት በጃቸዉ ብር አዉተዉ ሲሄዱ በር አካባቢ በሚኖሩ ሌቦች የተሰረቁትን ማን ይቁጠረዉ እንዲሁም በተለይ በሲስተም ከመላኩ በተጨማሪ በራሳቸዉ ጥፋት ሳይለኩት ይቀርና አልተላከም ተብለዉ ሲጠየቁ ተቃጥሏል እንደገና ትመርመር