(መሠረት ሚድያ)- ከአዲስ አበባ 40 ኪ/ሜ ገደማ ርቀት ላይ የምትገኘው የጫንጮ ከተማ ከቅርብ አመታት ወዲህ ሰላም ርቋታል። ተስማሚ አየር እና መልካም ገፀ ምድር ያላት የኦሮሚያ ክልሏ ጫንጮ በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (መንግስት ኦነግ ሸኔ የሚለው) እና በመንግስት ሀይሎች መካከል በሚደረግ ግጭት ምክንያት ፀጥታዋ ደፍርሷል።
ታድያ በከተማዋ ተወልደው ያደጉትም ይሆን ከሌላ ቦታ ወደ ከተማዋ ሄደው የሚኖሩ ነዋሪዎች ከቅርብ ወራት ወዲህ 'ሪጴ ሎላ' በተባሉ የኦሮሚያ ልዩ ሀይል አባላት አበሳቸውን እያዩ እንደሆነ መሠረት ሚድያ ባደረገው ክትትል ደርሶበታል።
"የምኖረውም ተወልጄ ያደኩትም እዚሁ ጫንጮ ከተማ ነው፣ ለስራ የተሰማራሁትም በሞባይል ሽያጭ ላይ ነው" የሚለው አንድ ስሙ እንዳይጠቀስ የጠየቀ ነዋሪ ሰሞኑን የመከላከያ ሰራዊት አባላት ከተማውን ለቀው ወደ ሌላ ቦታ መንቀሳቀሳቸውን ተከትሎ እነዚህ 'ሪጲ ሎላ' የተባሉት የመንግስት ሀይሎች የጫንጮን ነዋሪ እያሰቃዩ እንደሆነ ይናገራል።
Keep reading with a 7-day free trial
Subscribe to Meseret Media to keep reading this post and get 7 days of free access to the full post archives.